GridArt_20260921_170135539

​በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ታሪክ ውስጥ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቀጥሎ ከፍተኛውን ድርሻ ከሚይዙት እና በዎላይታ ዞን በኡማ ወንዝ ላይ ከተገነባው የጊቤ 3 (1887 ሜጋ ዋት) የኃይል ማመንጫ ማዕከል የሚመነጨው ብርሃን ዛሬ ላይ ድንበር አቋርጦ ጎረቤት ሀገራትን እያሞቀ ይገኛል።

በተለይም በዛሬው ዕለት መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (September 21, 2026) በወጡ አዳዲስ መረጃዎች እንደተመለከተው፣ ኬንያ ፓወር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ዩቲሊቲ ጋር በሐምሌ 2016 ዓ.ም ያደረገውን የኃይል አቅርቦት ስምምነት በማደስ የተያዘው የኮንትራት መጠን ከነበረበት 200 ሜጋ ዋት ወደ 400 ሜጋ ዋት በእጥፍ ከፍ አድርጎታል።

በዎላይታ ዞን በኡማ/ኦሞ ወንዝ ላይ ከተገነባው የጊቤ 3 (1887 ሜጋ ዋት) የኃይል ማመንጫ

ተጨማሪው ኤሌክትሪክ ከታህሳስ ወር ጀምሮ ወደ ኬንያ እንደሚደርስ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ፓወር የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

​ይህ የንግድ እመርታ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድገው የሚታመን ቢሆንም ከዚህ የቢሊዮኖች ብር የውጭ ምንዛሬ እና የንግድ ስኬት ጀርባ ግን ፕሮጀክቱ በሚገኝበት እምብርት ላይ የሚገኙት የዎላይታ እና የዳውሮ ሕዝቦች ከዓመታት በፊት ያነሷቸው እና እስካሁን ምላሽ ያላገኙ አንገብጋቢ የካሳ፣ የልማት እና የፍትህ ጥያቄዎች በጨለማ ውስጥ ተከድነው ይገኛሉ።

​በቢዝነስ ዴይሊ አፍሪካ ዘገባ መሠረት የኬንያ የኤሌክትሪክ ፍጆታ በሰኔ 2026 በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 12,792.42 ጊጋዋት-ሰዓት መድረሱን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ግዥም ወደ 1,584.45 ጊጋዋት-ሰዓት ከፍ በማለት ከኬንያ አጠቃላይ አቅርቦት 10 በመቶውን መሸፈኑ ተገልጿል።

ኬንያ ከሱዳን እና ከጅቡቲን በመልቀቅ የኢትዮጵያ ትልቁ የኤሌክትሪክ ደንበኛ መሆኗን ስትቀጥል በ2025/26 የበጀት ዓመት ከኬንያ ብቻ 15.62 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱ ተመላክቷል። ከጅቡቲ ጋር ተቀናጅቶ የሀገሪቱ የድንበር ተሻጋሪ የኤሌክትሪክ ንግድ 21.13 ቢሊዮን ብር ገቢ አስገኝቷል።

​ከዎላይታ ሶዶ እስከ ኬንያ (ሱስዋ) የተዘረጋው የ1,045 ኪሎ ሜትር የከፍተኛ ቮልቴጅ መስመር እስከ 2,000 ሜጋ ዋት ማስተላለፍ የሚችል ቢሆንም አሁን ላይ ወደ 400 ሜጋ ዋት ማደጉ ከጠቅላላ አቅሙ አንድ አምስተኛውን ብቻ የሚጠቀም መሆኑ ታይቷል።

አካባቢው ሀገሪቱን ከከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ማሟላት ባለፈ ለውጭ ገበያ የውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙ ማዕከላት አንዱ ቢሆንም፣ ግድቡ ሲጠናቀቅ ለዎላይታ ሶዶ ከተማ እና አካባቢው 50 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ለመስጠት ተገባ የነበረው ቃል እስካሁን ሳይከበር ቀርቷል።

ከዚህም በላይ በዎላይታ ዞን አጠቃላይ መብራት የሚያገኙት ሕዝቦች 20 በመቶ ገደማ ብቻ ሲሆኑ ዳውሮ ዞን ደግሞ ከዚህም የባሰ የጨለማ እና የበጀት ትኩረት ማነስ ሰለባ ሆኗል። የህዝቡ እጣ ፈንታ ከኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ውጭ መሆን፣ ከፍተኛ የወጣቶች ስራ አጥነት መስፋፋት፣ የልማት እንቅስቃሴዎች መጓተት እና መሰረተ ልማቶች አለመስራት ማዕከል ሆኖ ቀጥሏል።

በተጨማሪም ​ነገር ግን ከዚህ ግዙፍ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ገቢ ማግኛ ማዕከል ጀርባ ያለው እውነት እጅግ አሳዛኝ ነው። ከዓመታት በፊት በጊቤ 3 ማመንጫ እና በዎላይታ ላሾ ፓወር ስቴሽን ግንባታ ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች፣ በጤናቸው ላይ ቀጥተኛ ጉዳት እያደረሰባቸው የሚገኘውን አደጋ ተቋቁመው የሚኖሩ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ተገቢው የካሳ ክፍያ ተጠቃሚ አልሆኑም።

ቀደም ሲል ለተጎጂዎች የተሰጠው ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የካሳ ድጋፍ እንኳን ለተጎጂዎች ሳይደርስ በአብዛኛው በአመራሮች እጅ መግባቱ እና ገንዘቡን የተከለከሉት አካባቢው ነዋሪዎች እስከ ዞን ድረስ በአካልና በደብዳቤ ቢጠየቁም እስካሁን አንዳችም ምላሽ አላገኙም። “ከመላው ኢትዮጵያ አልፎ እስከ ጎረቤት ሀገራት ድረስ ብርሃን እየሰጠ ለራሱ ተገቢ ካሳ ሳይሰጥ አርሶ ከሚበላበት መሬቱ ተፈናቅሎ በጨለማ የሚገኘው ሕዝብ እስከመቼ ይገለላል?” የሚለው ጥያቄ መልስ አልባ ሆኖ ቀጥሏል።

​በሌላ በኩል በጊቤ 3 (ኡማ ወንዝ) ላይ የተገነባው ግድብ በፈጠረው ግዙፍ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ሳቢያ የዎላይታ እና የዳውሮ ህዝቦች የዘመናት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ሙሉ በሙሉ ተስተጉሏል። ነባሩ ማቋረጫ ድልድይ በሐይቁ መጥለቅለቁ ተከትሎ የሁለቱ ክልሎች ሕዝቦች እንቅስቃሴ በእጅጉ ከብዷል።

በዎላይታ ዞን በኡማ/ኦሞ ወንዝ ላይ ከተገነባው የጊቤ 3 (1887 ሜጋ ዋት) የኃይል ማመንጫ

​WT Media ከዓመት በፊት የተለያዩ ምሁራን በማናገር እንዳጠናቀረው ቱርክ እና ሌሎች ሀገራት ከ2 ኪሎ ሜትር በላይ ውሃ አሻጋሪ ድልድዮችን በዘመናዊ የምህንድስና ጥበብ ገንብተው እየተጠቀሙበት ቢሆንም በጊቤ 3 ሰው ሰራሽ ሐይቅ ላይ ግን የሁለቱን ሕዝቦች የንግድ፣ የትምህርት እና የማህበራዊ ግንኙነት አብሮነት የሚያስተሳስር ድልድይ በአስቸኳይ እንዲገነባ የቀረበው ጥያቄ በመንግስት በኩል ፍጹም ዝምታ ተገኝቶበታል።

የክልሎች አስተዳደር እና የፌዴራል መንግስት ለዚህ ማህበራዊ ቀውስ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለታቸው አጥፊ ክፍተት ሆኖ ቀጥሏል።

ኢትዮጵያ ከዎላይታ በሚመነጨው ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ንግድ ለኬንያ እና ለጎረቤት ሀገራት የምታደርገውን አቅርቦት በእጥፍ ከፍ አድርጋ በቢሊዮኖች የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬ እና ገቢ ስታስመዘግብ፣ በሀብቱ ባለቤት በሆነው በዎላይታ እና ዳውሮ እንዲሁም በሰፊው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚስተዋለው እጅግ የሰላ የልማት ኢፍትሃዊነት፣ ቸልተኝነት እና ስልታዊ መገለል አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

​አካባቢው ሀገሪቱን ከከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ማሟላት ባለፈ ለውጭ ገበያ የውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙ ማዕከላት አንዱ ቢሆንም የህዝቡ እጣ ፈንታ ግን ከኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ውጭ መሆን፣ ከፍተኛ የወጣቶች ስራ አጥነት መስፋፋት፣ የልማት እንቅስቃሴዎች መጓተት እና መሰረተ ልማቶች አለመስራት ማዕከል ሆኖ ቀጥሏል።

ከግቤ 3 እና ከዎላይታ ሶዶ ላሾ ኃይል ማከማቻ ማዕከል በሚገኘው ግዙፍ ገቢ ህዝቡ ተጠቃሚ እንዲሆን እና ተገቢው የልማት ምላሽ እንዲያገኝ ሲጠየቅ የነበረ ቢሆንም በመንግስት በኩል የትኩረት መንፈግ እና ዝምታ ብቻ ተሰጥቶታል።

​Voice of Marginalized Community – WT Media

#Ethiopia #southethiopia #wtmedia #Wolaita #Dawro #Gibe3