በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዎላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት በአንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ላይ የሁለት ዓመት ቀላል እስራት መፍረዱን ተከትሎ በነዋሪዎች፣ በሕግ ባለሙያዎች እና በዲጂታል መብት ተሟጋቾች ዘንድ በሐሳብ የመግለጽ ነፃነት ወሰን እና የክልሉ የጸጥታ መዋቅሮች ስማቸውን ደብቀው መንግስትን የሚተቹ አካላትን እንዴት እንደሚያጋልጡ በሚያሳዩ የቴክኖሎጂ መንገዶች ዙሪያ ከባድ ክርክሮች እየተደረጉ ይገኛሉ።
ሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአርባ ምንጭ ከተማ ያደረጉት ንግግር እና የዎላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ላይ ያስተላለፈው የ2 ዓመት ቀላል እስራት ውሳኔ፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለይም በዎላይታ ዞን ለዓመታት የዘለቀውን መዋቅራዊ የሐሳብ ማፈን፣ የመንግሥት ሌብነት እና የነፃ ትችት ምኅዳር መጥበብ ዳግም አደባባይ አውጥቶታል።
ይህ አፋኝ መዋቅር ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን WT Media ገና በማርች 2025 (በ2017 ዓ.ም.) ይፋ እንዳደረገው፤ በአካባቢው የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን፣ የመንግሥት ሌብነትንና ብልሹ አሠራርን ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ይፋ ለማድረግ የሚሞክሩ ወጣቶች፣ የመብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች ያለምንም ሕጋዊ መጥሪያ በፖለቲካ አመራር ትዕዛዝ ብቻ ለእስር፣ ለድብደባና ለስደት መዳረጋቸው የቆየ መዋቅራዊ በሽታ መሆኑን ማኅደሮቻችን ያረጋግጣሉ።
በማርች 2025 (በ2017 ዓ.ም.) በዎላይታ ተቀዛቅዞ የነበረው ሐሳባቸውን በልዩነት የሚገልጹ ወጣቶችን የማሰርና የመደብደብ ዘመቻ ዳግም ማገርሸቱን WT Media መዘገቡ ይታወሳል።
ለዚያ የእስር ዘመቻ መነሻ የነበረው፤ የሀገሪቱ ብሔራዊ ሚዲያ (ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን) “የማዕድን ስር ቁማርተኞች” በሚል ርዕስ በሠራው የምርመራ ዘገባ ላይ የዎላይታ ዞን አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ጴጥሮስ ወልደማርያም የሰጡት ምላሽ ነበር።
አስተዳዳሪው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የማዕድን ምዝበራና የአሠራር ጥሰት በተመለከተ ተጠይቀው፦ “እኛ እንዴት የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር በደብዳቤ እንጠይቃለን? እኛ አሁን በአፍ እየተደራረግን ነው” በማለት የሕዝብን ጥቅም የሚጎዳ አስተያየት መስጠታቸውን ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያ በሰላማዊ መንገድ ትችት የሰነዘሩ ወጣቶች ያለምንም ማስረጃና ከሳሽ በፖለቲካ አመራር ትዕዛዝ ብቻ ታስረው ነበር።
ያኔ በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተግባቦትና ጋዜጠኝነት መምህር ለWT Media በሰጡት ቃል፦ “ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት በሌለበት አስገድደው የማኅበራዊ ሚዲያዎቻቸውን እንዲከተሉ በማድረግ የግለሰቦችን ድምፅ ለማፈኛ የሚደረግ አዝማሚያ የመብት ጥሰት ከመሆኑ ባሻገር በአካባቢው ብልሹ አሠራር እንዲሰፍን ያደርጋል” በማለት የተናገሩት እውነት ዛሬም በተግባር እየታየ ይገኛል።
የ WT Media የምርመራ ክፍል በቅርቡ ባደረገው ማጣራት ዘገባ በጥቅሉ ሲገነባ የፈጀው ጠቅላላ ወጪ 80 ሚሊዮን ብር ብቻ የነበረው የዞኑ አስተዳደር ሕንጻ፣ በአሁኑ ወቅት የውጭና የውስጥ ቀለም ለመቀባት እንዲሁም አምፖል ለመቀየር ብቻ ከዞኑ ፋይናንስ እጅግ አስደንጋጭ የሆነ 200 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል።
ለዚህ መዋቅራዊ ምዝበራ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የወቅቱ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ ቢሮ መግባት ካቆሙ አሁን በትክክል 2 ወራት ተቆጥረዋል። በዚህ “የዕድሳት ስምምነት” ሰበብ በሕንጻው ውስጥ የሚሰሩ ከ10 በላይ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መደበኛ አገልግሎት አቋርጠው ይገኛሉ።
ከ200 ሺህ በላይ ከድግሪ እና ከዚያ በላይ የተማሩ የሥራ አጥ ወጣቶች ባሉበት ሕዝቡ በልማት በተጠማበት እና የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ በወቅቱ በማይከፈልበት ዞን ውስጥ 200 ሚሊዮን ብር ያለ ጨረታ ለኮንትራክተሮች በመስጠት ከከፍተኛ አመራሮችና ከፋይናንስ ኃላፊዎች ጋር ተባብሮ የሕዝብን ሀብት መቀራመት ግልጽ ወንጀል መሆኑን WT Media በሰነድ አረጋግጧል።
በዚህ መዋቅራዊ ሌብነት ላይ ሕዝቡ ተስፋ በቆረጠበት እና የምሁራን ቁጣ በበረታበት ወቅት የዎላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድቤት “ታ ዎላይታይ ጊታኔ ሚኖ” (Ta Wolaitay gitanne mino) እና “ለእውነት እንታገል” የተባሉ የፌክ የፌስቡክ ገጾችን (Fake Facebook Accounts) በመጠቀም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን ፎቶግራፍ በሐሳብ በማቀናጀት፣ የሐሰት መረጃ በማሰራጨት እና ሕዝባዊ አመጽ ለማነሳሳት ሞክሯል የተባለውን ግለሰብ በ2 ዓመት ቀላል እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን WT Media ከፍርድቤቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
እንደ WT Media መረጃ ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔ በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ታዛቢዎችን እያሳሰቡ ባሉ ሁለት ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ትኩረት እንዲያርፍ አድርጓል እነሱም የነፃ ትችት ምኅዳር መጥበብ እና በክልል ደረጃ የሚደረጉ የዲጂታል ክትትሎች የሚያስከትሉት ስጋት ናቸው።
የሕግ ተንታኞችና የመብት ተሟጋቾች እንደሚጠቁሙት፤ ሕገ-መንግሥቱ የሐሳብን ነፃነት በግልጽ ቢፈቅድም የክልሉ ባለሥልጣናት ግን የጥላቻ ንግግር እና የሳይበር ወንጀል አዋጆችን የፖለቲካ ተቃውሞዎችንና ገለልተኛ ዘገባዎችን ለማፈኛ መሣሪያነት እያዋሉት ይገኛሉ።
ታዛቢዎች እንደሚከራከሩት፤ በክልሉ ውስጥ በአስተዳደራዊ ሙስና፣ በሠራተኞች ደመወዝ መዘግየት እና በመሠረተ ልማት መጓደል ምክንያት የሕዝብ ብሶት በከፍተኛ ሁኔታ በበረታበት በዚህ ወቅት በባለሥልጣናት ላይ የሚሰነዘሩ ጠንካራ የፖለቲካ ትችቶችን “ሕዝብን ማነሳሳት” ወይም “ስም ማጥፋት” በሚሉ ክሶች መፈረጅ ዋነኛ ዓላማው ባለሥልጣናትን ከተጠያቂነት መከላከል ነው።
እውነተኛ የሐሳብ ነፃነት በሕዝብ ተሿሚዎች ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶችን መታገስ መቻል እንዳለበትና ፍርድ ቤቶችን ለፖለቲካዊ ቅጣት መጠቀም በአካባቢው ያለውን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት በእጅጉ እንደሚያዳክመው ተቺዎች ይገልጻሉ።
ከሕጋዊው ክርክር ባለፈ ይህ ክስተት የክልሉ የደኅንነት መዋቅር ስማቸውን ደብቀው የሚንቀሳቀሱ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን ማንነት እንዴት ሊያውቅ እንደቻለ በርካታ ጥያቄዎችን አስነስቷል።
በዲጂታል ምርመራ (Digital Forensics) ሂደት ውስጥ የመንግሥት የደኅንነት አካላት የአንድን አካውንት ባለቤት ለመለየት በተለምዶ የሚከተሏቸው የተራቀቁ የቴክኖሎጂ መንገዶች አሉ።
ግለሰቡ በእነዚህ የፌስቡክ ገጾች ላይ መረጃዎችን ሲጭን (Post ሲያደርግ) የተጠቀመበትን የኢንተርኔት መለያ አድራሻ (IP Address) ከመንግሥታዊው ኢትዮ ቴሌኮም የዳታ መረጃዎች ጋር በማመሳከር፣ በዚያ ሰዓት ያንን አይፒ የተጠቀመውን የሞባይል ዳታ ወይም የቤት ፋይበር ኢንተርኔት ባለቤት በቀጥታ መለየት ይቻላል።
ብዙ ጊዜ ስም-አልባ የፌክ ገጾች ሲከፈቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙበት የኋላ-ታሪክ ስልክ ቁጥር ወይም የኢሜይል አድራሻ (Recovery Email/Phone) ከግለሰቡ ትክክለኛ ማንነት ወይም በስሙ ከተመዘገበው ሲም ካርድ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ከሆነ በቀላሉ መጋለጥን ያስከትላል።
ተከሳሹ በሌላ ጥርጣሬ ወይም ክስ በቁጥጥር ሥር በሚውልበት ወቅት የተያዘው ስማርትፎን ወይም ኮምፒውተር በዲጂታል የፎረንሲክ መሣሪያዎች ሲፈተሽ በውስጡ ያሉ ንቁ አካውንቶች፣ የተቀመጡ የይለፍ ቃላት (Passwords) እና የተቀነባበሩ የፎቶግራፍ ፋይሎች በቀጥታ በመገኘታቸው ከገጹ ጋር ያለውን ቁርኝት ያረጋግጣሉ።
ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔ በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ለውጥና ፍትሕ እንዲመጣ ለሚታገሉ አካላት ዲጂታል ጥንቃቄ ማድረግ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ በክልሉ ያለውን የነፃነት ምኅዳር ይበልጥ አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት ክስተት ነው።
የሕግ ባለሙያዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በጥብቅ እንደሚያሳስቡት የፍትሕ አካላትና ፍርድ ቤቶች ፍጹም ገለልተኛ በመሆን የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ ያለባቸው እንጂ የባለሥልጣናት መበቀያና የፖለቲካ ፍላጎት ማስፈጸሚያ መጠቀሚያ መሆን የለባቸውም።
በአካባቢው ያሉ ዜጎችና አክቲቪስቶች ማኅበራዊ ሚዲያን በራሳቸው ትክክለኛ ስም ለመጠቀም የማይደፍሩት በዞኑም ሆነ በክልሉ እውነተኛ የሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ሙሉ በሙሉ በመታፈኑ ነው። ትችት በሰነዘሩ ቁጥር ሊደርስባቸው የሚችለውን ያልተገባ እስራት፣ ማደናቀፍና የተለያዩ አካላዊና ማኅበራዊ ጉዳቶችን አጥብቀው በመፍራት አማራጭ ስሞችን ለመጠቀም ቢገደዱም፣ የአሁኑ የፍርድ ቤት ውሳኔ ግን ያንንም በር ለመዝጋትና የፍርሃት ድባብ ለመፍጠር የታለመ ነው ሲሉ ብዙዎች በምሬት ይገልጻሉ።
በዚህ መዋቅራዊ ሌብነት ላይ ሕዝቡ ተስፋ በቆረጠበት እና የምሁራን ቁጣ በበረታበት ወቅት፣ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት “ታ ዎላይታይ ጊታኔ ሚኖ” እና “ለእውነት እንታገል” የተባሉ የፌክ የፌስቡክ ገጾችን በመጠቀም ባለሥልጣናትን ተችቷል የተባለውን ግለሰብ በ2 ዓመት ቀላል እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ የታፈነውን የነፃነት ምኅዳር ይበልጥ ያጠብቀዋል።
ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔ እና የመንግሥት የደኅንነት አካላት የአይፒ አድራሻ (IP Address)፣ የቴሌኮም ዳታ (Telecom Tracking) እና የስልክ ፍተሻዎችን (Device Forensics) በመጠቀም ስም-አልባ የሆኑ የፌክ አካውንቶችን ጭምር ለመከታተልና ለመቅጣት የሚያደርጉት ጥረት በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ የፍርሃት ድባብ ፈጥሯል። ዜጎችና አክቲቪስቶች ማኅበራዊ ሚዲያን በራሳቸው ትክክለኛ ስም ለመጠቀም የማይደፍሩት ትችት በሰነዘሩ ቁጥር ሊደርስባቸው የሚችለውን ሕገወጥ እስራት፣ ድብደባና ስደት አጥብቀው ስለሚፈሩ ነው።
የፍትሕ አካላትና ፍርድ ቤቶች ገለልተኛ በመሆን የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ ሲገባቸው የባለሥልጣናት መበቀያና የፖለቲካ ፍላጎት ማስፈጸሚያ መጠቀሚያ መሆናቸው የሕዝብን አመኔታ እያጠፋው ይገኛል።
WT Media በአካባቢው በሚስተዋሉ የሕዝብ ብሶቶች፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የመንግሥት ሌብነትና ፍርድ ቤቶች የባለሥልጣን መጠቀሚያ መሆንን በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ ተከታታይ የምርመራ ዘገባዎችን በሰነድና በማስረጃ አስደግፎ የሠራ መሆኑ ይታወቃል።